int(1)
Stay updated with the latest news and happenings.
በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ በስራና ክህሎት በአምስቱ ትኩረት መስኮች የዘርፉን ስራ በማጠናከር በሀገር ውስጥና ውጪ ስራ ዕድል ተጠቃሚነት በክህሎትና ኢኮኖሚ ተወዳዳሪ የሆነ ዜጋ መፍጠር ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን ይህ ስራ የታለመለትን ግብ እንዲመታ በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ በንግግራቸው፥ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር በክህሎት ልማትና ክህሎት መር ስራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም በመሳሰሉት አራት ትኩረት መስኮች የሚሰራ የለውጡ ትሩፋት ተቋም ጠቁመው የክልሉ መንግስት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ የላቀ ውጤት መምጣቱን አስገንዝበዋል።
የዘርፉን ስራ በይበልጥ በታችኛው መዋቅር በልዩ ትኩረት መፈጸም እንዳለበት ያብራሩ አቶ ሰለሞን ሶካ፤ አንድ ምርት በአንድ መንደር፣የእሴት ሰንሰለት የስራ ዕድል ፈጠራ፣ ኢ-መደበኛ የስራ ዕድል ወደ መደበኛ ስራ መለወጥ፣የስራ ማዕከላት ሪፎርም ትግበራ እንዲሁም በዲጂታል ስርአት ላይ ትኩረት ማድረግ በልዩ ትኩረት መፈጸም የሚገባቸው የዘርፉ ትኩረት መስኮች መሆናቸውን አስረድተዋል።
የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ የመድረኩን ዓላማ ስገልጹ ባለፈው በጀት አመት በስራና ክህሎት የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡን አውስተው በዘርፉ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ የተሰሩ ዘርፈ ብዙ ስራዎች በቀጣይም በላቀ ቅንጅት እንዲፈጸም ለማነሳሳት ነው ብለዋል።
ባለፈው በጀት አመት በዘርፉ ሀገር ውስጥና ውጪ ስልጠናዎችን በመስጠትና የስራ ዕድል በመፍጠር በተሰሩ ስራዎች ስኬታማ አፈጻጸም ተመዝግቧል ያሉት ኃላፊዋ፤ የሌሎች ባለድርሻ አካላት አፈጻጸም እንደተጠበቀ ሆኖ መንግስት ብድር በማመቻቸት በማቴሪያልም አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም የማምረቻና መሸጫ ቦታዎችን በማዘጋጀት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ አድርጎ ነው ውጤቱ የተገኘው ብለዋል።
ወ/ሮ ሀገረጽዮን አክለውም በቀጣይ ከወትሮው ይልቅ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ድርሻችንን ለመወጣት በቁርጠኝነት መሰለፍ ይገባናል በሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
Comments
Lowo geeshsha danchahona konninnilla hanaffe
Danchaho
Add a Comment